ዛሬም እንደገና፦
ለማቅረብ ምስጋና
ነዋያችን በዝቶ ጃፓን ደርስዋልና!
*
እች ነች ጭዋታ
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ...
አፈ ጮማይትዋ፦
...
ነጻ አውጪ ክሊንተን
እንክዋን ደረስሽልን፤
ያል አንቺ ቡራኬ
እኔም ሆንኩ ጥላቴ
ምንም አይሆንልን።
....
ድምጸ አሜሪካንም
አይዞሽ አታስቢ፣ አይከለከልም፦
ያለምን ባንክ ብቻ አፉን አስይዥልን፦
ሌላውም አይቀባጥር ኦሮሞ ኦጋዴን
ኤሳት ሆነ ሌላ ፦እሳት አይንዛብን፦
ያም ሆነ ይህኛው፦ ሸብር ፈጣሪ ነው ካልወደደን እኛን ፣
ለዜና ፋብሪካ ፣ከእኔና አንቺ ወዲያ፦ እኛው እንበቃለን።
ታውቂው የለም እንዴ፣ ከባድ ሸክም አለን
ያከባቢው ፖሊስ ፣ ወኪል ያሜሪካን፦
የለም የሚታዘዝ ፦ እንደኔ የሚሆን፦
ሆኖም፦ ይመስለኛል፣ ለኔ ብተይልኝ...ነጻ - አውጭነቱን
ታሪክ ያለኝ ሎሌ፦ትላንት ሱማሌ፦ ዛሬ ደግሞ ሱዳ ን፤
ጠባየ ጎደሎ፦ የትላንት ወዲያውን
አታንሽው ግድየለም እናሳየዋለን፦ይቀር በሆዳችን
ብዙ ነው ሥራችን።
አለያም አይበጀን፦አይበጅም
አይ ካልሽኝ ኣይሆንም ፤
እንደ ብርቱክዋንዋ የስውር ወዳጅሽ፦
ዶሮ ሲያረጉ አይታ፣ ብየ፣ እንዳልተርትብሽ፤
ጨው ሁኚ ይልቁን፦ ስትዪ ለራስሽ
ተረት አረጋለሁ፦ተረት እወዳለሁ፣
አላስቸግርሽም፦ ጣፍጪ ብየሻለሁ።
ሃገሬ ሰፊ ነው በገቢያ ላይ ወጥትዋል፣
ከሩቅ ምስራቅ ሆነ ከህንድም ይመጣል፤
የአረብ ባለጸጋም ፣ገዥው ተትረፍርፍዋል።
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤
ሰሞኑን በዛብን፤ ኧረ ምነው ፈካ!
ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ ፦ የ ኮ በ ለ ለ ው ን!
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን።
በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን ፤ መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ፦ ማከማቻ
*
-ኤርትራን እወራለሁ
-አባይን ገድባለሁ
-ግብጥን ነክሻለሁ
-ሱዳን እሄዳለሁ
ሰላም መጥናለሁ
-ሱማሌ እቆያለሁ።
-ዋጋ መቆ ጣጠር
ትቻለሁ ፡ ለቃለሁ
-ካቶሊክ ሆኛለሁ ፤
ነጋዴ አግብቼያለሁ
- ይቅርታ ብያለሁ፤
ደርግን እፈታለሁ።
*
ደግሞም ድንቅ እንቅ ይበላችሁ
አልፌ ተርፌ ጃፓንን ረዳለሁ
ለታሪክና ፌዝ ይመዝገብ በቶሎ፦ በጥብቅ አዝዣለሁ። (ይኀ ሁሉ፤)
እንዳንረሳሳ ፡ ጅራፍ እባላለሁ
ገርፌ ጮሃለሁ፤
ብሬን አሸሻለሁ፡
ዋ ብቻ ብያለሁ፤
ቀልቤን እንዳትገፉ፦ ሃብቴን እንዳትነኩ
ባህር ማዶ ያለውን፤ በየፈረንጅ ባንኩ።
(ላለ ማለት ሽር ጉዱ!)
*
ሌቱ እስኪነጋ ለት
ቀን እስኪወጣ ለት
ያገሬ ሰው እንደሁ
ተኝ ሲሉት ተኛለሁ
ቁም ሲሉት ቆማለሁ።
እኔ ግን እነሁ
አድንቁ ይግረማችሁ ፤
ቀኔ የሞላ ለት
ክጫካ ወጥቼ፤
አሜሪካን ወዶኝ
እንግሊዝ ዶልቼ፤
ከተማ ገብቼ፦
ሙሉ ሃያ ዓመት ገዛሁኝ
የምሥራች በሉኝ።
ነገም ዛሬም እኔ ፤ አርባ እሞ ላለሁ፤
እከርማለሁ ገና ከንጉሥ እበልጣለሁ፤
ቤን አሊ ጋዳፌ ሙባረክ አይደለሁ
ባስራ ሁለት ቢላ መብላት ተክኛለሁ።
እንደኔ ዓይነት ምላስ፤
ከሰንበር የሚለይ
ባሳብ በትካዜ፤
ባገር በወንዜም ላይ፤
ኣንድም ቀን አይታይ፤
መለስ ዘና ዘና፤ ደሞም፤
ካስፈለገም
የሚል ቆጣ ቆጣ ፦
የሚያስደነግጥም በጣቶች ቆረጣ፤
ሃያ ምላስ አለኝ
በመላው አፍሪቃ፤
ፍጡም ወደር የለኝ።
ለሁሉም መልስ ያለው፤
መለስ እባላለሁ
ባባቴ ዜናዊ ፤
የዜና ፋብሪካ፦
ወሬ እወልዳለሁ
ዕጡብ ድንቅ በሉኝ፤
ዘላለም ኖራ ለ ሁ።
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤
ሰሞኑን በዛብን፤ ኧረ ምነው ፈካ!
ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ ፦ የ ኮ በ ለ ለ ው ን!
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን።
በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን ፤ መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ፦ ማከማቻ
*
ሞልትዋል፤ተትረፍርፍዋል፤
ይቀጥላል ገና
የ መለስ፦ የመልስ ጋጋታ-- የፋብሪካ ዜና።
No comments:
Post a Comment