- -

ከሃይል ንቀት ወደ ዕውቀትና ንቃት ለህዝባዊ ዕድገት

ዕው

ስማ ስሚ ስሙ በስመ አብ ቢስሚላሂ በሉ፤

በቅላጼ መልክት፤ ይታደስ-ይቀደስ ትውልደ-ብርሃኑ፤

በተቻለው መጠን፤ በተፈለገ ለት፤ ቀን ይወጣል አሉ።

እንደ መሃል ምሥራቅ፤ አፍሪቃ ሰሜኑ፤

ኢትዮጵያም ይደርሳል ፅዋው መኅበሩ፤

Beautiful Minds of Addis Tiwlid 2012 1*)

Search

Monday, September 19, 2011

የአቶ አንዱዓለም አራጌ፣ የአቶ እስክንድር ነጋና የሌሎች ተከሳሾች የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ

የአቶ አንዱዓለም አራጌ፣ የአቶ እስክንድር ነጋና የሌሎች ተከሳሾች የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ
source: http://www.ethioguardian.com/news.php


“አንድ ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ የምናገረው ሃሳብ አለኝ፡፡ እየተፈፀመ ያለው ተግባር የተቃዋሚ ፖለቲካውን ለማፈን የተወሰደ እርምጃ ነው፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ፍርድ ቤቱ የፈለገውን እርምጃ፤ ሞትም ቢሆን መውሰድ ይችላል፡፡ ሌላ የምሰጠው አስተያየት የለኝም” አቶ አንዱዓለም አራጌ
“በ2004 ዓ.ም. በሀገሪቱ ውስጥ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በቡድን ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ ማስረጃ አግኝቼባቸዋለው” በማለት በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር ያዋላቸው የፓርቲ አመራሮችና ጋዜጠኛ አራዳ የፌደራል መ/ደ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት ቀርበዋል፡፡ 


በቅድምያ በችሎቱ የቀረበው እውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነበር፡፡ አጃቢ ፖሊሶች ማንም ሰው ወደ እስረኛው ሆኖ ወደ ችሎቱ እንዳይቀርብ በመከልከላቸው የችሎቱን ሂደት ማንም አልተከታተለውም፡፡ ሆኖም ጋዜጠኞች ዳኛው ጋር በመቅረብ መከልከላችንን አስረድተው ወደ ችሎቱ ለመግባት ለማስፈቀድ ችለዋል፡፡ ቀደም ሲል የቀረበው እስክንድር ነጋ ፖሊሲ የጠየቀውን የ28 ቀን ምርመራ ጊዜ ተጠይቆበት ለጥቅምት 02 /2004 ዓ.ም. በ8፡00 ሰዓት ተቀጥረዋል፡፡

በመቀጠል አቶ ዘመኑ ሞላ የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የተከሰሱበትን ጉዳይ ያውቁ እንደሆነ ጠይቆዋቸው፣ ፖሊስ እንደ ነገረኝ በሽብርተኝነት ተጠርጥረህ ነው ብሎኛል፣ እኔ ስለ ሽብር ተግባር የማውቀው ነገር የለም፡፡ በቅርቡ የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር ነኝ፡፡ ፓርቲያችን መስከረም 21 ቀን 2004 ዓ.ም. ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቀን ነበር፡፡ ከዚህ ውጭ የማውቀው ነገር የለም ብለዋል፡፡

ቀጥሎ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባላት የሆኑት አቶ አሳምነው እና አቶ ናትናሄል መኮንን በቅድም ተከተላቸው በዳኛው በአቶ ሙሉ ክንፈ ፊት ቀርበው፣ በሽብር ተግባር ተጠርጥረሃል ከመባል ውጭ የፈፀምነው ወንጀል የለም ብለው መልሰዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ በመስጠት ለጥቅምት 02 /2004 በ8፡00 ሰዓት ቀጥሮዋቸዋል፡፡

በመጨረሻም የቀረበው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲሁም የመድረክ ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ አንዱዓለም አራጌ ናቸው፡፡ ፍርድ ቤቱ በምን እንደተያዙ ጠይቋዋቸው ፖሊሰ በሽብር ተግባር ነው ብሎኛል ሲሉ መልሰዋል፡፡ ፖሊሲ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆቦታል፣ የሚሰጡት ሃሳብ አሎት ተብሎ ሲጠየቁ አቶ አንዱዓለም  “አንድ ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ የምናገረው ሃሳብ አለኝ፡፡ እየተፈፀመ ያለው ተግባር የተቃዋሞ ፖለቲካውን ለማፈን የተወሰደ እርምጃ ነው፡፡ ከእንግዲ ወዲያ ፍርድ ቤቱ የፈለገውን እርምጃ ሞትም ቢሆን መውሰድ ይችላል፡፡ ሌላ የምሰጠው አስተያየት የለኝም” ሲሉ መልሰዋል፡፡ በመቀጠልም ዳኛው የምጠይቆት የእርሶን መብት ለማስክበር ነው፡፡ በሚናገሩት ነገር እርምጃ መውሰድ ይችላል፡፡ ፍ/ቤቱ ሊያከብሩ ይገባል ሲሉ ዳኛው አቶ ሙሉ ክንፈ ተናግረዋል፡፡ ፍ/ቤት በነጻ የዳኝነት ስርዓት የሚያከናውን ነው፡፡ በፍርድ ቤቱ አያምኑም? ሲሉ የተናገሩ ሲሆን አቶ አንዱዓለም በመጨረሻም “እኔ ነጻ ነው ብዬ አላስብም” ብለዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል
መስከረም 04/ 2004

No comments:

Post a Comment

1*)


"When the idea formed of Divinity is the fruit of true spiritual culture, its intimate re-action on the inner perfection is at once beneficial and beautiful. All things assume a new form and meaning in our eyes when regarded as the creatures of forecasting design, and not the capricious handiwork of unreasoning chance. The ideas of wisdom order, and adaptative forethought,—ideas so necessary to the conduct of our own actions, and even to the culture of the intellect,—strike deeper root into our susceptible nature, when we discover them everywhere around us. The finite becomes, as it were, infinite; the perishable, enduring; the fleeting, stable; the complex, simple,—when we contemplate one great regulating Cause on the summit of things, and regard what is spiritual as endlessly enduring. Our search after truth, our striving after perfection, gain greater certainty and consistency when we can believe in the existence of a Being who is at once the source of all truth, and the sum of all perfection. The soul becomes less painfully sensible of the chances and changes of fortune, when it learns how to connect hope and confidence with such calamities. The feeling of receiving everything we possess from the hand of love, tends no less to exalt our moral excellence and enhance our happiness. Through a constant sense of gratitude for enjoyment—through clinging with fond trustfulness to the object towards which it yearns, the soul is drawn out of itself, nor always broods in jealous isolation over its own sensations, its own plans, hopes, and fears. Should it lose the exalting feeling of owing everything to itself, it still enjoys the rapture of living in the love of another,—a feeling in which its own perfection is united with the perfection of that other being. It becomes disposed to be to others what others are to it; it would not that they too should receive nothing but from themselves, in the same way that it receives nothing from others."

Wilhelm von Humboldt, The Limits of State action; 1792(CHAPTER VII.
Religion)

The Synthesis