- -

ከሃይል ንቀት ወደ ዕውቀትና ንቃት ለህዝባዊ ዕድገት

ዕው

ስማ ስሚ ስሙ በስመ አብ ቢስሚላሂ በሉ፤

በቅላጼ መልክት፤ ይታደስ-ይቀደስ ትውልደ-ብርሃኑ፤

በተቻለው መጠን፤ በተፈለገ ለት፤ ቀን ይወጣል አሉ።

እንደ መሃል ምሥራቅ፤ አፍሪቃ ሰሜኑ፤

ኢትዮጵያም ይደርሳል ፅዋው መኅበሩ፤

Beautiful Minds of Addis Tiwlid 2012 1*)

Search

Thursday, July 14, 2011

ተ ረ ሳ ኣ!...ተ ረ ሳ... እንዴ?

የመልስ ጋጋታ፤ የፋብሪካ ዜና የሰ ሞኑ ገብያ IV(1 
*
ተ ረ ሳ ኣ!...ተ ረ ሳ  እንዴ?
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤   
ሰሞኑን በዛብን፤  ኧረ ምነው ፈካ! 

ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ ፦ የ ኮ በ ለ ለ ው ን! 
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን።

በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን ፤ መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ፦ ማከማቻ
*
እች ነች ጭዋታ
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ...

ተ ረ ሳ ኣ!
ተ ረ ሳ  እንዴ?
 
ተረሳ እንዴ ትላንት
የባንዲራው ንቀት
የጨርቃ ጨርቅ ዕውቀት
ታሪክ ከመቶ ዓመት
አለፈው በድንገት
ሊያምረን ነው ዘንድሮ የቆየው ጅግንነት
የሚኒሊኩ ድል፦ ያድዋው ጦርነት

ውሃው የዮሃነስ፦ጥናት ከሃይማኖት
ፋሲል ቤተ መንግሥት
ላሊበላ፦ ዕውቀት ቤተ ክህነት
ግእዝ ፊደል ቅኔ ትምህርት
ያክሱም ሥልጣኔ ኅውልት።

ኧረ ያስተዛዝባል መሰንበት መቆየት
ጃንሆይ አልቀሩም በጃፓኑ ምኞት
ባልተሳካላቸው በከሸፈው ዕድገት።

ደርግም ሊነሳ ነው በመልካም አንደበት
በፈረንጁም ቢሆን የመሳቅያ ተረት፤
መንግስቱ ኃ/ማ ቢፈለግም ለሞት
ደቡብ ሱዳን መጣ፤ ይፋም ባይነገር፦ ቤት የሚሠራለት።


ጉድ! ዘንድሮ ነው ማለት!

ስልጣኑ ድብዳብ፦ከርሞ ሲሰነብት፦
እየከጀለን ነው የቆየ ጀግንነት
ከኔ ወዲያ መሪ ተባለ ያላፍረት

ለማስታወስ ያህል፦
እናቅ የለም እንዴ በርከት ያለ ተረት
የወጋ ቢረሳ
የተወጋ አይረሳ
ውሃ ካፈሰሱት ሀገር ከበተኑት
አይታፈስ መቼም አይገኝ ብልሃት።

ስንቱን አተራምሶ ባገር በጎረቤት፤
ለማን እንዲሆን ነው ይኅ ሁሉ መልክት
ሆቸ ጉድ! ተባለልን ዛሬ፦ እንጣጥ  እንጣጥ  ማለት፦
ባልተገባ ዕብሪት በኢምንት ዕድገት፤
ወይስ ጨዋታ ነው የህሊና ትምህርት
አዲሱ ብልሃት ላለማመን ስህተት፤
የሰሞኑ ምንባብ ተሃድሶ ዕውቀት
አሰሱን ገሰሱን ሸፋፍኖ ለማምረት።
እንደ ተለመደው፦ ይች ሃገር፦ ተላላ ሞኝ ናት
የሠራላት ቀርቶ የሰራላት በላት፤
መልከ ጥፉን ክስተት፦በስም ይደግፉ ተረት፦ 
በተሃድሶ ስም ታሸጎ ለገቢያ የማይራራው አንጀት፤
አይ ንቀት አይ ድፍረት ሥልጣን ለማሰንበት።


ይልቅስ፦ ዕውነቱን ተናግሮ ማደር የመሸበት፤
ሲሆን ለመሀተብ፦ ባይሆን ለህሊና ዕረፍት።

ዳግም ሲደጋገም፤ የፈረንጁ፦ የሚያሰቀው ተረት፤
ደርግ  መቼም ወታደር እኮ ነው፦ ተብሎ ያለቀለት
 የት ያውቃል ብልሃት።
ይልቅስ ጉድ ጉድ የሚያሰኘው፦
ጉድጓዱ እዚህ ላይ ነ ው፤
አይን እጥብ አድርጎ ሲያሞኙ፦ በስመ አንድነት፤
ታድሶ በመጣው፦ ንቃት አይሉት፦ የሰው፦የትውስት፦
 የአይምሮ ንቀት!

በቃ በ ቃ ተ ዉት!
ይህኛውን እንኳን ተዉት….. ለሚያውቅበት!

ፅድቁ ቀርቶብኝ፦በወግ - በኮነኑኝ፦ይሉ
ይህም ሆነ ሌላ  አልሆነም በሙሉ
ከመዝገበ ቃላት ይሰረዝ ዘንድ  ቃሉ
ኢትዮጵያን ከረሃብ ያገናኘው ሁሉ፤

በነበረን በውነት፦
ከፍ ያለ እንኳን ምኞት፤
ምክንያት ተደርድሯል ሆንዋል የህዝብ ብዛት
ላይወጣ ከሃገር ረሃብ ድህነት ሞት

እርዱን ድረሱልን ይባላል ሰሞኑን፦የታል ምንተ ዕፍረት?

መንገድ ተዘርግቶ፦ፎቁ ተተርትሮ ከተማ  ግንባታ፤
 ባረብ በህንድ ገንዘብ በምራብ ዕርዳታ
ለምለሚቷ መሬት ለባዕድ አምርታ
በሥልጣኑ መንደር፦የጥቂቶች ገነት ሆናም ሃገሪቷ።

*
እስቲ ይሁን ግድ የለም
በተረፈው ገንዘብ
ዓባይም ይገደብ፤

ልናይ  ቆይተናል
ተስፋ አይከለከል፤
አዋቂ እንደሚለው፦ ባይነፈግ እንኳን ሁለተኛም ዕድል፤
ጨዋታ ብጤ ነው፦ ለወሬም አይመስልም፦
ያንድነቱንስ ቀልድ፦በቀና ህሊናም አይገዛውም ማንም፤
ብለን እንደምድም።
*

ቀላል ነው ምክንያቱ፦
ያስታውስ ባለቤቱ....
****


እንዳንረሳሳ ፡ ጅራፍ እባላለሁ
ገርፌ ጮሃለሁ፤
ብሬን አሸሻለሁ፡
ዋ  ብቻ ብያለሁ፤
ቀልቤን እንዳትገፉ፦ ሃብቴን እንዳትነኩ
 ባህር ማዶ ያለውን፤
የተከማቸውን፤ በየፈረንጅ ባንኩ።
****
ሌቱ እስኪነጋ ለት
ቀን እስኪወጣ ለት
ያገሬ ሰው እንደሁ
ተኝ ሲሉት ተኛለሁ
ቁም ሲሉት ቆማለሁ።

እኔ ግን እነሁ
አድንቁ ይግረማችሁ  ፤
ቀኔ የሞላ ለት
 ክጫካ ወጥቼ፤
አሜሪካን ወዶኝ
እንግሊዝ ዶልቼ፤
ከተማ ገብቼ፦
ሙሉ ሃያ ዓመት ገዛሁኝ
የምሥራች በሉኝ።
ነገም ዛሬም እኔ ፤ አርባ እሞ ላለሁ፤
እከርማለሁ ገና  ከንጉሥ እበልጣለሁ፤
ቤን አሊ ጋዳፌ ሙባረክ አይደለሁ
ባስራ ሁለት ቢላ መብላት ተክኛለሁ።

እንደኔ ዓይነት ምላስ፤ 
                     ከሰንበር የሚለይ
ባሳብ በትካዜ፤
ባገር በወንዜም ላይ፤
                ኣንድም ቀን አይታይ፤
መለስ ዘና ዘና፤ ደሞም፤
ካስፈለገም
የሚል ቆጣ ቆጣ ፦
የሚያስደነግጥም በጣቶች ቆረጣ፤
                   ሃያ ምላስ አለኝ
በመላው አፍሪቃ፤
                ፍጡም ወደር የለኝ።
ለሁሉም መልስ ያለው፤
                         መለስ እባላለሁ
ባባቴ ዜናዊ ፤ 
የዜና ፋብሪካ፦ 
                      ወሬ እወልዳለሁ
ዕጡብ ድንቅ በሉኝ፤ 
                           ዘላለም ኖራ ለ ሁ።

***
በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን  መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ማከማቻ
 *
ሞልትዋል፤ተትረፍርፍዋል፤

ይቀጥላል ገና
የመልስ ጋጋታ-- የፋብሪካ ዜና --የሰሞኑ ገቢያ

Tuesday, July 12, 2011

ATLANTA 2011 - ለአትላንታ ማስታወሻ

ለዘንድሮው አትላንታ ማስታወሻ *1!

አዲስ የኳስ ጨዋታ ተፈጥሮ፦ ባለአስራ አንድ አባላት፦
ሁለት ቡድን ይሁን ሶስት፦ ያልታወቀ ያለበት፤
የሶስተኛው ቡድን ማንነት፤
አስራ አንድ ይሁን፦አስራ ሁለት፦

ይዘቱ ያልለየለት።

የትም ዞረ የትም አስራ ሁለተኛው ለየት ይላል፦
የመሰወር ዘይቤን ተክኖታል ።


ዓፈ ቀላጤ ግልጋሎቱ፦ ስውር ሆኖም፦ ለሁሉም፤
ወገን ለይቶ ጭዋታም አይሻም።

ባሻው ቡድን ገብቶ ሲጫወት፦
ሁሉም እሱን ብቻ ሆነና፦ የሚያደምጡት፤
ሌላው አስራ አንዱ ቢጯጯሁ፦ ማንን ሊሰማ ማን፦
ጭዋ ታው ቀርቶ፦ የጨረባ ተዝካር ሲሆን።

እርሱ ደግሞ ልዩ ጥበቡና ማዕረጉ፦
ቡድናት እንዳይሸናነፉ ማድረጉ።
በአጥቂ ጥበቡ ላንደኛው ግብ ሲያሰገባ፦
ሌላው ሲያኮርፍበት ያንን ሲያግባባ፦
አቻ ለአቻ እየሆኑ ጀንበር ጠለቀ ጠባ።

እንዲያም ሲል ለተመልካች ሆነ ተጫዋች፦
ሆነና፦ መላ ቅጥ ያጣ አሰላች፤
ጨዋታው ግጥሚያ አይሉት ውድድር፦
የእርስ በርስ፦ ሆያ ሆዬ የመንደር፤
አወይ እያበገነ ሲያስመርር፦
አስራ ሁለተኛው በመሃል ግርግር፦
መሪ ተዋናይ ሆኖ ሲቀር።

ግሩም ድንቅ
ያንተ ስራ ይልቅ!

እንድያ እንዲያ ሲል ግማሽ ምዕተ ዓመት አለፈን፦
የዕውነት ግብ ማስገባት አቅቶን፤
ሁለት ይሁን ሶስት ማወቅ ተስኖን፦
የ ኳስ ምስጢረ ስላሴ ሳይገባን፦
የ ጭዋ ተው  ቡድናችን

ኣወይ ጉዳችን፦

ሲሆን፦ ማዘን፤
 ለዘመኑ ጅግኖቻችን።

Friday, July 8, 2011

የፋብሪካ ዜና፦የዜና ፋብሪካ፦የሰ ሞኑ ገብያ III ...VOA =V...OH...OH....A

-reproduced here with an update-

የመልስ ጋጋታ፤ የፋብሪካ ዜና የሰ ሞኑ ገብያ  
*
„ነፃ አውጪ ክሊንተን„ II
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤   
ሰሞኑን በዛብን፤  ኧረ ምነው ፈካ! 

ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ ፦ የ ኮ በ ለ ለ ው ን! 
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን።

በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን ፤ መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ፦ ማከማቻ
*
እች ነች ጭዋታ
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ...
*
አፈ ጮማይትዋ፦
...
ነጻ አውጪ ክሊንተን
                          እንክዋን ደረስሽልን፤
ያል አንቺ ቡራኬ 
እኔም ሆንኩ ጥላቴ
                                ምንም አይሆንልን።
*
ድምጸ አሜሪካንም
አይዞሽ አታስቢ፣ አይከለከልም፦
ያለምን ባንክ ብቻ አፉን አስይዥልን፦
ሌላውም አይቀባጥር ኦሮሞ ኦጋዴን
ኤሳት ሆነ ሌላ ፦እሳት አይንዛብን፦
ያም ሆነ ይህኛው፦ ሸብር ፈጣሪ ነው ካልወደደን እኛን ፣


ብዬሽ እኮ ነበር

*
ጎሽ የኔ ኮንጆ፦ እንደ ባለቤትሽ ነውር የሌለብሽ
የሰው ማስፈራራሪያ ምክር የሚሆንሽ፤
ውነትም ፈጣን ነሽ፦ጨው ሳይሆን፦ ወርቅ ጠባይ አለሽ ፤
ከሎሌ እንክዋን ሳይቀር፦ትምህርት ቀሳሚ፦ጎበዝ እመቤት ነሽ
ብሶት ከዛቻ ጋር፦ፖለቲክ የገባሽ፤
ሃገር በጨረታ የለውም ግዴታ ብዬ ያወጋሁሽ
  ባአፉ ካላወራ ፡ጣቱን ካልጻፈበት ለሚነሳው ዕረፈት ፦
ኑሮና ሰቆቃህ ፦ይሁን ጭለማ ቤት 
ብዬ፦ የኔን ሽብርተኞች፦ በላክዋቸው ማግስት
 
ያንችን ቀባጣሪ ልክ አስገባሽልኝ
የዛቻ ፍሬዬን እንዳመርት አረግሽኝ።
 
አሁን፦ምናባቱ ቻይና፦ በርቺ እንበርታ
አፍሪካን አይገዛም በዋዛ ፈዛዛ፦ ካንች ወዲያ ጨረታ፤
ህንዱንም ሌላውን እንሰራለታለን፦አይዞኝ ዶሮ ማታ።
ቀስ በቀስ ግድየለም፦ ሁሉም ይደረሳል
ለጊዜው ባሰቸኩዋይ ሱዳን ይጠራናል!

እንደተባባልነው፦በኔ በኩል እንደሁ ዝግጅቱ ጦፍዋል፤
የወታደር ዕዙም ባዲስ ተፐውዝዋል
እንደምትረጂው፦ስልጣንና ትዛዝ አብሮ አደግ ያውካል
ሰንባች አዛዦቹ ጡረታ ወጥታዋል።

በነገራችን ላይ፦ ውሃ ቅዳ መልስ ላንቺም አይሁንብሽ፦
ለዛ ቀባጣሪ ለDAVID (1 መተኪያ፦ በረከት ስሞንን አሁን ልላክልሽ!?
ሲያስፈልግ በስደት፦ ጡረታውም ደርስዋል ትንሽም ይራቀኝ፤
ደሞ ሱም እንደሰው፦ ኣለሁ አለሁ ብሎ ነገር ሳይፈልገኝ!
ብቻ!
እንዳንረሳሳ ፡ ጅራፍ እባላለሁ
ገርፌ ጮሃለሁ፤
ብሬን አሸሻለሁ፡
ዋ  ብቻ ብያለሁ፤
ቀልቤን እንዳትገፉ፦ ሃብቴን እንዳትነኩ
 ባህር ማዶ ያለውን፤
የተከማቸውን፤ በየፈረንጅ ባንኩ።
****

Wednesday, July 6, 2011

የፋብሪካ ዜና፦የዜና ፋብሪካ፦የሰ ሞኑ ገብያ II

" ነፃ አውጪ አሜሪካ"
-reproduced here with an update-

የመልስ ጋጋታ፤ የፋብሪካ ዜና የሰ ሞኑ ገብያ  

ዛሬም እንደገና፦
ለማቅረብ ምስጋና
ነዋያችን በዝቶ ጃፓን ደርስዋልና!
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤   
ሰሞኑን በዛብን፤  ኧረ ምነው ፈካ


ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ 
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን።

በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን  መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ማከማቻ
 *
እች ነች ጭዋታ
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ...
*
በያን ሰሞንማ፣ ቢሆንም  ባይሆንም ጅግኖች ፈጥሬያለሁ
ወዳጄ አሜ ሪካን፦ተው አይሆንም ብሎ ለትምርት  ልኬያለሁ

ባገር ብከለክል እንዳይተነፍሱ፡ ሂደዋል  ዘምተዋል እሱን ሊያሸብሩ
ተገላግያለሁ ከኔ ከወረዱ  እሱኑ ይበለው፦ ሰፊ ነው ሃገሩ።
ብርቱን ብትደፍር ሰቆቃዋን ረስታ
ያ ከይሲ ወገኔ፦ ስዬ ቢከተልም፦ በታምቡር በዕልልታ፤
ሽብር ቢፈጥሩበት በዛው ባሜሪካ
የመሬን ሥልጣንና ሃይሌን፦ ጫፌንም አይነካ፤
  አለኝ ነው ስማይ፤ እኔን የሚተካ
ወዳጅም ጠላትም ይፈንጥዝ ያስካካ፤.
  ሲበጅ ሲጠነሰስ ተንኮል ባሜሪካ፤
አይበርደኝ አይሞቀኝ ለነገው ፋሲካ።

ብዙ ወዳጅ አለኝ ካስፈለገም ደግሞ
የሚያስተዳድረኝ ከዛሬ አልፎ ከርሞ።
የመንፈስ በር ሳይቀር ከፍቶ ከሚገባው
ጠይቆ ጠያይቆ እኔን እንክዋን ሳይቀር ዕውነት ያገረው
ሀገሬን ለማቅናት፦ ከብሮ ለሚከብረው
ብሩን ያለ ሃሳብ በገፍ ያፈሰሰው፤
እምነት በምድር ላይ ጥንት የመነጨበት፦ማሰብ ሲጀምር ሰው፦
የከርሞው ህንድ አለ፦ታምር የሚሰራው፤
ውሎም አድሮ ቢሆን፦በጥቂቱ ዛሬ፦ የትልቁ ነዋይ፦ ባለቤት የሆነው፤
ችግር ያልተለየው ትግስቱን አስፍቶ፤የበረታ እንደሆን በእግዜር ብቻ አማሮ
እንዳገሬ ህዝብ ወይ ዕድሌ ብሎ ያላንዳች እሮሮ፦
መናጢ ድሃና ያበጠው በለሃብት
ተቃቅፎ ያለ ጥል፦ዛሬ ሚኖርበት፦
የዘንድሮው ህንድ የጥቂቶች ገነት፤
ሃሳብ ጤና ይስጥልኝ፦ከጎን ቆሞልኛል፦
ይንቅ-ያመናቅር፦ አዲስ-ፍቅር፦ይዞኛል።

ህንድን ሲሻገሩ ሞልትዋል ዕሩቅ ምስራቅ
ኣታምጣው ነው እንጂ፦የተፈጥሮን ቁጣ፦ ጃፓንን የሚያስንቅ፤
ይሁን፦ገና የሚዳሩት፦ ወይንም ወዳጅ ያደረግሁት፦
የጥንቱ የደጉ፦ የኮንፊሱስ ሃገር፤ እንደ ኔው ተማሪ የትላንት ኮሚኒስት
ታታሪው ቻይና አለ፦የገቢያው አዳራሽ ምድርን ያደረጋት።
ስንቱን ልደርድረው ኮርያ ነው ታይላንድ ድፍን አስያ ነው
ላውሮፓ አሜሪካ መቃብር ቆፋሪው፦ ወዳጄ ሚሆነው።

የመሃሉን ምሥራቅ፦ የአረቡን ተዉት፦ ጎረቤት ጌታዬን
ለሥልጣን ስፈጠር፦ ሁሉንም የሚያውቀው ጉድና ጉድግዋዴን
ያልተሰወረ ነው ፦ ከሳሩም ቅጠሉ ፦ ጠይቁ አላሙዲን።   
  
*
እናም፦ያ ህንድ ጋዜጠኛ እንዳስለፈለፈኝ፤ ብዙም ሳልቀባዥር፦
ልደምድም ባጭሩ፦ ሳላባክን ምስጢር፤
ጉልበት ብትሉ፦ የነዋይ፦ የሥልጣኑ ነገር
እንደ ከበሮው ነው፦ በሰው እጅ ያምር፤
እንክዋን ለሚሰማ ለጠላቴም ይቅር።
መርምሬ አውቀዋለሁ
አልፌበታለሁ፤
አይ ከንቱ! ነው ከቶ፤
ሰው ካገሩ ወጥቶ...

ቢጋልቡት ፈረሰ ቢጭኑት አህያ፦
ባይ ነኝ ባለ ተራ፦ ሰርዶ ከኔ ወዲያ።

*

ብቻ!

እንዳንረሳሳ ፡ ጅራፍ እባላለሁ
ገርፌ ጮሃለሁ፤
ብሬን አሸሻለሁ፡
ዋ  ብቻ ብያለሁ፤
ቀልቤን እንዳትገፉ፦ ሃብቴን እንዳትነኩ
 ባህር ማዶ ያለውን፤
የተከማቸውን፤ በየፈረንጅ ባንኩ።

******************************************************

„ነፃ አውጪ ክሊንተን
*

እች ነች ጭዋታ
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ...
*
አፈ ጮማይትዋ፦
...
ነጻ አውጪ ክሊንተን
                          እንክዋን ደረስሽልን፤
ያል አንቺ ቡራኬ 
እኔም ሆንኩ ጥላቴ
                                ምንም አይሆንልን።
....
ድምጸ አሜሪካንም
አይዞሽ አታስቢ፣ አይከለከልም፦
ያለምን ባንክ ብቻ አፉን አስይዥልን፦
ሌላውም አይቀባጥር ኦሮሞ ኦጋዴን
ኤሳት ሆነ ሌላ ፦እሳት አይንዛብን፦
ያም ሆነ ይህኛው፦ ሸብር ፈጣሪ ነው ካልወደደን እኛን ፣
ለዜና ፋብሪካ ፣ከእኔና አንቺ ወዲያ፦ እኛው እንበቃለን።


ታውቂው የለም እንዴ፣ ከባድ ሸክም አለን
ያከባቢው ፖሊስ ፣ ወኪል ያሜሪካን፦
የለም የሚታዘዝ ፦ እንደኔ የሚሆን፦
ሆኖም፦ ይመስለኛል፣ ለኔ ብተይልኝ...ነጻ - አውጭነቱን 
ታሪክ ያለኝ ሎሌ፦ትላንት ሱማሌ፦ ዛሬ ደግሞ ሱዳ ን፤
ጠባየ ጎደሎ፦ የትላንት ወዲያውን 
አታንሽው ግድየለም እናሳየዋለን፦ይቀር በሆዳችን 
ብዙ ነው ሥራችን።

አለያም አይበጀን፦አይበጅም
አይ ካልሽኝ ኣይሆንም
እንደ ብርቱክዋንዋ የስውር ወዳጅሽ፦
ዶሮ ሲያረጉ አይታ፣ ብየ፣ እንዳልተርትብሽ፤
ጨው ሁኚ ይልቁን፦ ስትዪ ለራስሽ 
ተረት አረጋለሁ፦ተረት እወዳለሁ፣ 
አላስቸግርሽም፦ ጣፍጪ ብየሻለሁ።

  ሃገሬ ሰፊ ነው በገቢያ ላይ ወጥትዋል፣
ከሩቅ ምስራቅ ሆነ ከህንድም ይመጣል፤
የአረብ ባለጸጋም ፣ገዥው ተትረፍርፍዋል።
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤   
ሰሞኑን በዛብን፤  ኧረ ምነው ፈካ! 

ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ ፦ የ ኮ በ ለ ለ ው ን! 
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን።

በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን ፤ መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ፦ ማከማቻ
*
 -ኤርትራን እወራለሁ

-አባይን ገድባለሁ

-ግብጥን ነክሻለሁ

-ሱዳን እሄዳለሁ
      ሰላም መጥናለሁ

-ሱማሌ  እቆያለሁ።

-ዋጋ  መቆ ጣጠር
ትቻለሁ ፡ ለቃለሁ

-ካቶሊክ ሆኛለሁ ፤ 
ነጋዴ አግብቼያለሁ

- ይቅርታ ብያለሁ፤
ደርግን እፈታለሁ።
*
ደግሞም ድንቅ እንቅ ይበላችሁ
አልፌ ተርፌ ጃፓንን ረዳለሁ
ለታሪክና ፌዝ
ይመዝገብ በቶሎ፦ በጥብቅ አዝዣለሁ።
 (ይኀ  ሁሉ፤)

እንዳንረሳሳ ፡ ጅራፍ እባላለሁ
ገርፌ ጮሃለሁ፤
ብሬን አሸሻለሁ፡
ዋ  ብቻ ብያለሁ፤
ቀልቤን እንዳትገፉ፦ ሃብቴን እንዳትነኩ
ባህር ማዶ ያለውን፤ በየፈረንጅ ባንኩ።

(ላለ ማለት  ሽር ጉዱ!)

*
ሌቱ እስኪነጋ ለት
ቀን እስኪወጣ ለት
ያገሬ ሰው እንደሁ
ተኝ ሲሉት ተኛለሁ
ቁም ሲሉት ቆማለሁ።

እኔ ግን እነሁ
አድንቁ ይግረማችሁ  ፤
ቀኔ የሞላ ለት
 ክጫካ ወጥቼ፤
አሜሪካን ወዶኝ
እንግሊዝ ዶልቼ፤
ከተማ ገብቼ፦
ሙሉ ሃያ ዓመት ገዛሁኝ
የምሥራች በሉኝ።
ነገም ዛሬም እኔ ፤ አርባ እሞ ላለሁ፤
እከርማለሁ ገና  ከንጉሥ እበልጣለሁ፤
ቤን አሊ ጋዳፌ ሙባረክ አይደለሁ
ባስራ ሁለት ቢላ መብላት ተክኛለሁ።

እንደኔ ዓይነት ምላስ፤ 
                     ከሰንበር የሚለይ
ባሳብ በትካዜ፤
ባገር በወንዜም ላይ፤
                ኣንድም ቀን አይታይ፤
መለስ ዘና ዘና፤ ደሞም፤
ካስፈለገም
የሚል ቆጣ ቆጣ ፦
የሚያስደነግጥም በጣቶች ቆረጣ፤
                   ሃያ ምላስ አለኝ
በመላው አፍሪቃ፤
                ፍጡም ወደር የለኝ።
ለሁሉም መልስ ያለው፤
                         መለስ እባላለሁ
ባባቴ ዜናዊ ፤ 
የዜና ፋብሪካ፦ 
                      ወሬ እወልዳለሁ
ዕጡብ ድንቅ በሉኝ፤ 
                           ዘላለም ኖራ ለ ሁ።
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤   
ሰሞኑን በዛብን፤  ኧረ ምነው ፈካ! 

ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ ፦ የ ኮ በ ለ ለ ው ን! 
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን። 
በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን  መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ማከማቻ
1*)


"When the idea formed of Divinity is the fruit of true spiritual culture, its intimate re-action on the inner perfection is at once beneficial and beautiful. All things assume a new form and meaning in our eyes when regarded as the creatures of forecasting design, and not the capricious handiwork of unreasoning chance. The ideas of wisdom order, and adaptative forethought,—ideas so necessary to the conduct of our own actions, and even to the culture of the intellect,—strike deeper root into our susceptible nature, when we discover them everywhere around us. The finite becomes, as it were, infinite; the perishable, enduring; the fleeting, stable; the complex, simple,—when we contemplate one great regulating Cause on the summit of things, and regard what is spiritual as endlessly enduring. Our search after truth, our striving after perfection, gain greater certainty and consistency when we can believe in the existence of a Being who is at once the source of all truth, and the sum of all perfection. The soul becomes less painfully sensible of the chances and changes of fortune, when it learns how to connect hope and confidence with such calamities. The feeling of receiving everything we possess from the hand of love, tends no less to exalt our moral excellence and enhance our happiness. Through a constant sense of gratitude for enjoyment—through clinging with fond trustfulness to the object towards which it yearns, the soul is drawn out of itself, nor always broods in jealous isolation over its own sensations, its own plans, hopes, and fears. Should it lose the exalting feeling of owing everything to itself, it still enjoys the rapture of living in the love of another,—a feeling in which its own perfection is united with the perfection of that other being. It becomes disposed to be to others what others are to it; it would not that they too should receive nothing but from themselves, in the same way that it receives nothing from others."

Wilhelm von Humboldt, The Limits of State action; 1792(CHAPTER VII.
Religion)

The Synthesis