-reproduced here with an update-
የመልስ ጋጋታ፤ የፋብሪካ ዜና ፤ የሰ ሞኑ ገብያ *
„ነፃ አውጪ ክሊንተን„ II
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤
ሰሞኑን በዛብን፤ ኧረ ምነው ፈካ!
ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ ፦ የ ኮ በ ለ ለ ው ን!
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን።
በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን ፤ መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ፦ ማከማቻ
*
እች ነች ጭዋታ
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ...
*
አፈ ጮማይትዋ፦
...
ነጻ አውጪ ክሊንተን
እንክዋን ደረስሽልን፤
ያል አንቺ ቡራኬ
እኔም ሆንኩ ጥላቴ
ምንም አይሆንልን።
*
ድምጸ አሜሪካንም
አይዞሽ አታስቢ፣ አይከለከልም፦
ያለምን ባንክ ብቻ አፉን አስይዥልን፦
ሌላውም አይቀባጥር ኦሮሞ ኦጋዴን
ኤሳት ሆነ ሌላ ፦እሳት አይንዛብን፦
ያም ሆነ ይህኛው፦ ሸብር ፈጣሪ ነው ካልወደደን እኛን ፣
ብዬሽ እኮ ነበር…
*
ጎሽ የኔ ኮንጆ፦ እንደ ባለቤትሽ ነውር የሌለብሽ
የሰው ማስፈራራሪያ ምክር የሚሆንሽ፤
ውነትም ፈጣን ነሽ፦ጨው ሳይሆን፦ ወርቅ ጠባይ አለሽ ፤
ከሎሌ እንክዋን ሳይቀር፦ትምህርት ቀሳሚ፦ጎበዝ እመቤት ነሽ ።
ብሶት ከዛቻ ጋር፦ፖለቲክ የገባሽ፤
ሃገር በጨረታ የለውም ግዴታ ብዬ ያወጋሁሽ።
ባአፉ ካላወራ ፡ጣቱን ካልጻፈበት ለሚነሳው ዕረፈት ፦
ኑሮና ሰቆቃህ ፦ይሁን ጭለማ ቤት
ብዬ፦ የኔን ሽብርተኞች፦ በላክዋቸው ማግስት፤
ያንችን ቀባጣሪ ልክ አስገባሽልኝ የዛቻ ፍሬዬን እንዳመርት አረግሽኝ።
አሁን፦ምናባቱ ቻይና፦ በርቺ እንበርታ
አፍሪካን አይገዛም በዋዛ ፈዛዛ፦ ካንች ወዲያ ጨረታ፤
ህንዱንም ሌላውን እንሰራለታለን፦አይዞኝ ዶሮ ማታ።
ቀስ በቀስ ግድየለም፦ ሁሉም ይደረሳል
ለጊዜው ባሰቸኩዋይ ሱዳን ይጠራናል!
እንደተባባልነው፦በኔ በኩል እንደሁ ዝግጅቱ ጦፍዋል፤
የወታደር ዕዙም ባዲስ ተፐውዝዋል
እንደምትረጂው፦ስልጣንና ትዛዝ አብሮ አደግ ያውካል
ሰንባች አዛዦቹ ጡረታ ወጥታዋል።
በነገራችን ላይ፦ ውሃ ቅዳ መልስ ላንቺም አይሁንብሽ፦
ለዛ ቀባጣሪ ለDAVID (1 መተኪያ፦ በረከት ስሞንን አሁን ልላክልሽ!?
ሲያስፈልግ በስደት፦ ጡረታውም ደርስዋል ትንሽም ይራቀኝ፤
ደሞ ሱም እንደሰው፦ ኣለሁ አለሁ ብሎ ነገር ሳይፈልገኝ!
ብቻ!
እንዳንረሳሳ ፡ ጅራፍ እባላለሁ
ገርፌ ጮሃለሁ፤
ብሬን አሸሻለሁ፡
ዋ ብቻ ብያለሁ፤
ቀልቤን እንዳትገፉ፦ ሃብቴን እንዳትነኩ
ባህር ማዶ ያለውን፤የተከማቸውን፤ በየፈረንጅ ባንኩ።
****
No comments:
Post a Comment