- -

ከሃይል ንቀት ወደ ዕውቀትና ንቃት ለህዝባዊ ዕድገት

ዕው

ስማ ስሚ ስሙ በስመ አብ ቢስሚላሂ በሉ፤

በቅላጼ መልክት፤ ይታደስ-ይቀደስ ትውልደ-ብርሃኑ፤

በተቻለው መጠን፤ በተፈለገ ለት፤ ቀን ይወጣል አሉ።

እንደ መሃል ምሥራቅ፤ አፍሪቃ ሰሜኑ፤

ኢትዮጵያም ይደርሳል ፅዋው መኅበሩ፤

Beautiful Minds of Addis Tiwlid 2012 1*)

Search

Wednesday, July 6, 2011

የፋብሪካ ዜና፦የዜና ፋብሪካ፦የሰ ሞኑ ገብያ II

" ነፃ አውጪ አሜሪካ"
-reproduced here with an update-

የመልስ ጋጋታ፤ የፋብሪካ ዜና የሰ ሞኑ ገብያ  

ዛሬም እንደገና፦
ለማቅረብ ምስጋና
ነዋያችን በዝቶ ጃፓን ደርስዋልና!
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤   
ሰሞኑን በዛብን፤  ኧረ ምነው ፈካ


ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ 
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን።

በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን  መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ማከማቻ
 *
እች ነች ጭዋታ
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ...
*
በያን ሰሞንማ፣ ቢሆንም  ባይሆንም ጅግኖች ፈጥሬያለሁ
ወዳጄ አሜ ሪካን፦ተው አይሆንም ብሎ ለትምርት  ልኬያለሁ

ባገር ብከለክል እንዳይተነፍሱ፡ ሂደዋል  ዘምተዋል እሱን ሊያሸብሩ
ተገላግያለሁ ከኔ ከወረዱ  እሱኑ ይበለው፦ ሰፊ ነው ሃገሩ።
ብርቱን ብትደፍር ሰቆቃዋን ረስታ
ያ ከይሲ ወገኔ፦ ስዬ ቢከተልም፦ በታምቡር በዕልልታ፤
ሽብር ቢፈጥሩበት በዛው ባሜሪካ
የመሬን ሥልጣንና ሃይሌን፦ ጫፌንም አይነካ፤
  አለኝ ነው ስማይ፤ እኔን የሚተካ
ወዳጅም ጠላትም ይፈንጥዝ ያስካካ፤.
  ሲበጅ ሲጠነሰስ ተንኮል ባሜሪካ፤
አይበርደኝ አይሞቀኝ ለነገው ፋሲካ።

ብዙ ወዳጅ አለኝ ካስፈለገም ደግሞ
የሚያስተዳድረኝ ከዛሬ አልፎ ከርሞ።
የመንፈስ በር ሳይቀር ከፍቶ ከሚገባው
ጠይቆ ጠያይቆ እኔን እንክዋን ሳይቀር ዕውነት ያገረው
ሀገሬን ለማቅናት፦ ከብሮ ለሚከብረው
ብሩን ያለ ሃሳብ በገፍ ያፈሰሰው፤
እምነት በምድር ላይ ጥንት የመነጨበት፦ማሰብ ሲጀምር ሰው፦
የከርሞው ህንድ አለ፦ታምር የሚሰራው፤
ውሎም አድሮ ቢሆን፦በጥቂቱ ዛሬ፦ የትልቁ ነዋይ፦ ባለቤት የሆነው፤
ችግር ያልተለየው ትግስቱን አስፍቶ፤የበረታ እንደሆን በእግዜር ብቻ አማሮ
እንዳገሬ ህዝብ ወይ ዕድሌ ብሎ ያላንዳች እሮሮ፦
መናጢ ድሃና ያበጠው በለሃብት
ተቃቅፎ ያለ ጥል፦ዛሬ ሚኖርበት፦
የዘንድሮው ህንድ የጥቂቶች ገነት፤
ሃሳብ ጤና ይስጥልኝ፦ከጎን ቆሞልኛል፦
ይንቅ-ያመናቅር፦ አዲስ-ፍቅር፦ይዞኛል።

ህንድን ሲሻገሩ ሞልትዋል ዕሩቅ ምስራቅ
ኣታምጣው ነው እንጂ፦የተፈጥሮን ቁጣ፦ ጃፓንን የሚያስንቅ፤
ይሁን፦ገና የሚዳሩት፦ ወይንም ወዳጅ ያደረግሁት፦
የጥንቱ የደጉ፦ የኮንፊሱስ ሃገር፤ እንደ ኔው ተማሪ የትላንት ኮሚኒስት
ታታሪው ቻይና አለ፦የገቢያው አዳራሽ ምድርን ያደረጋት።
ስንቱን ልደርድረው ኮርያ ነው ታይላንድ ድፍን አስያ ነው
ላውሮፓ አሜሪካ መቃብር ቆፋሪው፦ ወዳጄ ሚሆነው።

የመሃሉን ምሥራቅ፦ የአረቡን ተዉት፦ ጎረቤት ጌታዬን
ለሥልጣን ስፈጠር፦ ሁሉንም የሚያውቀው ጉድና ጉድግዋዴን
ያልተሰወረ ነው ፦ ከሳሩም ቅጠሉ ፦ ጠይቁ አላሙዲን።   
  
*
እናም፦ያ ህንድ ጋዜጠኛ እንዳስለፈለፈኝ፤ ብዙም ሳልቀባዥር፦
ልደምድም ባጭሩ፦ ሳላባክን ምስጢር፤
ጉልበት ብትሉ፦ የነዋይ፦ የሥልጣኑ ነገር
እንደ ከበሮው ነው፦ በሰው እጅ ያምር፤
እንክዋን ለሚሰማ ለጠላቴም ይቅር።
መርምሬ አውቀዋለሁ
አልፌበታለሁ፤
አይ ከንቱ! ነው ከቶ፤
ሰው ካገሩ ወጥቶ...

ቢጋልቡት ፈረሰ ቢጭኑት አህያ፦
ባይ ነኝ ባለ ተራ፦ ሰርዶ ከኔ ወዲያ።

*

ብቻ!

እንዳንረሳሳ ፡ ጅራፍ እባላለሁ
ገርፌ ጮሃለሁ፤
ብሬን አሸሻለሁ፡
ዋ  ብቻ ብያለሁ፤
ቀልቤን እንዳትገፉ፦ ሃብቴን እንዳትነኩ
 ባህር ማዶ ያለውን፤
የተከማቸውን፤ በየፈረንጅ ባንኩ።

******************************************************

„ነፃ አውጪ ክሊንተን
*

እች ነች ጭዋታ
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ...
*
አፈ ጮማይትዋ፦
...
ነጻ አውጪ ክሊንተን
                          እንክዋን ደረስሽልን፤
ያል አንቺ ቡራኬ 
እኔም ሆንኩ ጥላቴ
                                ምንም አይሆንልን።
....
ድምጸ አሜሪካንም
አይዞሽ አታስቢ፣ አይከለከልም፦
ያለምን ባንክ ብቻ አፉን አስይዥልን፦
ሌላውም አይቀባጥር ኦሮሞ ኦጋዴን
ኤሳት ሆነ ሌላ ፦እሳት አይንዛብን፦
ያም ሆነ ይህኛው፦ ሸብር ፈጣሪ ነው ካልወደደን እኛን ፣
ለዜና ፋብሪካ ፣ከእኔና አንቺ ወዲያ፦ እኛው እንበቃለን።


ታውቂው የለም እንዴ፣ ከባድ ሸክም አለን
ያከባቢው ፖሊስ ፣ ወኪል ያሜሪካን፦
የለም የሚታዘዝ ፦ እንደኔ የሚሆን፦
ሆኖም፦ ይመስለኛል፣ ለኔ ብተይልኝ...ነጻ - አውጭነቱን 
ታሪክ ያለኝ ሎሌ፦ትላንት ሱማሌ፦ ዛሬ ደግሞ ሱዳ ን፤
ጠባየ ጎደሎ፦ የትላንት ወዲያውን 
አታንሽው ግድየለም እናሳየዋለን፦ይቀር በሆዳችን 
ብዙ ነው ሥራችን።

አለያም አይበጀን፦አይበጅም
አይ ካልሽኝ ኣይሆንም
እንደ ብርቱክዋንዋ የስውር ወዳጅሽ፦
ዶሮ ሲያረጉ አይታ፣ ብየ፣ እንዳልተርትብሽ፤
ጨው ሁኚ ይልቁን፦ ስትዪ ለራስሽ 
ተረት አረጋለሁ፦ተረት እወዳለሁ፣ 
አላስቸግርሽም፦ ጣፍጪ ብየሻለሁ።

  ሃገሬ ሰፊ ነው በገቢያ ላይ ወጥትዋል፣
ከሩቅ ምስራቅ ሆነ ከህንድም ይመጣል፤
የአረብ ባለጸጋም ፣ገዥው ተትረፍርፍዋል።
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤   
ሰሞኑን በዛብን፤  ኧረ ምነው ፈካ! 

ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ ፦ የ ኮ በ ለ ለ ው ን! 
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን።

በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን ፤ መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ፦ ማከማቻ
*
 -ኤርትራን እወራለሁ

-አባይን ገድባለሁ

-ግብጥን ነክሻለሁ

-ሱዳን እሄዳለሁ
      ሰላም መጥናለሁ

-ሱማሌ  እቆያለሁ።

-ዋጋ  መቆ ጣጠር
ትቻለሁ ፡ ለቃለሁ

-ካቶሊክ ሆኛለሁ ፤ 
ነጋዴ አግብቼያለሁ

- ይቅርታ ብያለሁ፤
ደርግን እፈታለሁ።
*
ደግሞም ድንቅ እንቅ ይበላችሁ
አልፌ ተርፌ ጃፓንን ረዳለሁ
ለታሪክና ፌዝ
ይመዝገብ በቶሎ፦ በጥብቅ አዝዣለሁ።
 (ይኀ  ሁሉ፤)

እንዳንረሳሳ ፡ ጅራፍ እባላለሁ
ገርፌ ጮሃለሁ፤
ብሬን አሸሻለሁ፡
ዋ  ብቻ ብያለሁ፤
ቀልቤን እንዳትገፉ፦ ሃብቴን እንዳትነኩ
ባህር ማዶ ያለውን፤ በየፈረንጅ ባንኩ።

(ላለ ማለት  ሽር ጉዱ!)

*
ሌቱ እስኪነጋ ለት
ቀን እስኪወጣ ለት
ያገሬ ሰው እንደሁ
ተኝ ሲሉት ተኛለሁ
ቁም ሲሉት ቆማለሁ።

እኔ ግን እነሁ
አድንቁ ይግረማችሁ  ፤
ቀኔ የሞላ ለት
 ክጫካ ወጥቼ፤
አሜሪካን ወዶኝ
እንግሊዝ ዶልቼ፤
ከተማ ገብቼ፦
ሙሉ ሃያ ዓመት ገዛሁኝ
የምሥራች በሉኝ።
ነገም ዛሬም እኔ ፤ አርባ እሞ ላለሁ፤
እከርማለሁ ገና  ከንጉሥ እበልጣለሁ፤
ቤን አሊ ጋዳፌ ሙባረክ አይደለሁ
ባስራ ሁለት ቢላ መብላት ተክኛለሁ።

እንደኔ ዓይነት ምላስ፤ 
                     ከሰንበር የሚለይ
ባሳብ በትካዜ፤
ባገር በወንዜም ላይ፤
                ኣንድም ቀን አይታይ፤
መለስ ዘና ዘና፤ ደሞም፤
ካስፈለገም
የሚል ቆጣ ቆጣ ፦
የሚያስደነግጥም በጣቶች ቆረጣ፤
                   ሃያ ምላስ አለኝ
በመላው አፍሪቃ፤
                ፍጡም ወደር የለኝ።
ለሁሉም መልስ ያለው፤
                         መለስ እባላለሁ
ባባቴ ዜናዊ ፤ 
የዜና ፋብሪካ፦ 
                      ወሬ እወልዳለሁ
ዕጡብ ድንቅ በሉኝ፤ 
                           ዘላለም ኖራ ለ ሁ።
*
የመልስ ጋጋታ፤ የወሬ፦የዜና ፋብሪካ፤   
ሰሞኑን በዛብን፤  ኧረ ምነው ፈካ! 

ዳቦ አይሆን ነገሩ፤ አይተካ ዶላሩን፦
ለክፉ ቀን ብሎ ፦ የ ኮ በ ለ ለ ው ን! 
እንዳባይ ወንዝ ውሃ ያልተገደበውን፦
ላገር ብልጥግና አልሆንም ያለውን። 
በላይ በላዩ የወሬ ጉርሻ
ለምን ይሆን፦ ለችግር ቅርሻ
በላይ በላዩ ዛቻ
ለምን ይሆን  መሰንበቻ
ነዋይ ሥልጣን ማከማቻ

No comments:

Post a Comment

1*)


"When the idea formed of Divinity is the fruit of true spiritual culture, its intimate re-action on the inner perfection is at once beneficial and beautiful. All things assume a new form and meaning in our eyes when regarded as the creatures of forecasting design, and not the capricious handiwork of unreasoning chance. The ideas of wisdom order, and adaptative forethought,—ideas so necessary to the conduct of our own actions, and even to the culture of the intellect,—strike deeper root into our susceptible nature, when we discover them everywhere around us. The finite becomes, as it were, infinite; the perishable, enduring; the fleeting, stable; the complex, simple,—when we contemplate one great regulating Cause on the summit of things, and regard what is spiritual as endlessly enduring. Our search after truth, our striving after perfection, gain greater certainty and consistency when we can believe in the existence of a Being who is at once the source of all truth, and the sum of all perfection. The soul becomes less painfully sensible of the chances and changes of fortune, when it learns how to connect hope and confidence with such calamities. The feeling of receiving everything we possess from the hand of love, tends no less to exalt our moral excellence and enhance our happiness. Through a constant sense of gratitude for enjoyment—through clinging with fond trustfulness to the object towards which it yearns, the soul is drawn out of itself, nor always broods in jealous isolation over its own sensations, its own plans, hopes, and fears. Should it lose the exalting feeling of owing everything to itself, it still enjoys the rapture of living in the love of another,—a feeling in which its own perfection is united with the perfection of that other being. It becomes disposed to be to others what others are to it; it would not that they too should receive nothing but from themselves, in the same way that it receives nothing from others."

Wilhelm von Humboldt, The Limits of State action; 1792(CHAPTER VII.
Religion)

The Synthesis