„አህያውን ፈርቶ ዳውላውን!“
ኢትዮጵያን ዛሬ ማን ነው የሚያስተዳድራት ? ኢህአዴግ በአሜሪካና በምእራብ አውሮፓ፣ አንድ ምሁር እንዳሉት፣ በሚተነፍሰው ኦክሲጂን ካልተደገፈ አንድ ቀን ኣያድርም። ግፋ ቢል የቻይና ጉያ ውስጥ ገብቶ ይለይለታል። ያኔ ደግሞ ቻይናን የማይወዷት እዚሁ አካባቢ ጉድ ጉድ ማለታቸው አይቀርም! ይህ ሆኖ ሳለ ፣ በተለይ ከውጭ ሆነው ኢህአዴግን የሚታገሉት የፖለቲካ ሃይሎች ዋናው ትግላቸው ፣ ኢህአዴግን በህይወት የሚያቆዩት እነዚህ ሃይሎች ላይ ለምን እንደማያቶኩር በመገረም የተፈለገ ምሳሌ ነው። „አህያውን ፈርቶ ዳውላውን!“
እንዳው ለምሳሌ ያህል፣ ሰሞኑን ካራቱሪ የሚባለውን በሃገራችን መሬት ከተስፋፉት የባእድ ባለጸጎች ውስጥ አንዱ፣ የሚፈጽመውን በደል ለማጋለጥ የማደንቀው የነጻነት ታጋይ ኦባንግ ሜቶ ይህ እንዴት እንደሚደረግ፣ አሳይቶናል። ውጤት የሚሰጥ የዚህ ዓይነት የማያቋርጥ ዘመቻ እንዴት እንደሚደረግ ደግሞ ብዙ ሌሎች ልምዶችም አሉ ? ኢህአዴግን ለመታገል ሁሉም በየፊናው ብዙ ጉልበትና ሃይል ያፈሳል። ኢህኣዴግ ከወዳጆቹ የሚተነፍሰው አየር እንዳያገኝ ስር የሰደደና የተቀላጠፈ ዘመቻ ከማድረግ ተቃዋሚ ሃይሎችን፣ /በተለይ የዲያስፖራውን / 21 ዓመት ሙሉ ግን፣ ምን ሲያግዳቸው እንደቆየ አይገባኝም! ችግሩ ድንቁርና ይሁን ሌላ፣ ወይስ አሻንጉሊትነት፣ ስላልገባኝ፣ ሃገር ወዳድ ነኝ የሚል ሁሉ ከራሱ አዕምሮ ጋር ይነጋገር ዘንድ የመጣ ሃሳብ ነው! ሕ. ብ.
*
እስቲ እናውራ ካልን፣
አህያውን ትቶ አይሁን ዳውላውን፣
ከልብ ካለቀሱ ዕንባ አይገድም በሉን !
ቀሪውን ለማንበብ :
No comments:
Post a Comment