The 117th Anniversary of the Battle of Adwa
1st March 1896 – is The Dawn – The Rainbow - of All Coloured Peoples of the Planet Earth!
*
A pair of words on the articles below commemorating the 117th anniversary of the battle of Adwa:
http://ethioforum.org/the-117th-anniversary-of-the-battle-of-adwa-by-robele-ababya/
ይህ ጽሁፍ ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድላችንን- የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካና የመላ ጥቁር ህዝብ መኩሪያ ሆኖ ከፍ ብሎ የሚታየውን የጸረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ድል - 117ኝውን የአድዋ ድል መታሰቢያ አስመልክቶ ያነበብኩት ሁለተኛው ነው!
ሌላው
http://www.ethiomedia.com/addis/5681.html
የአድዋው ድል መሪ የታልቁ አጼ ሚኒሊክና የሌሎች ጀግኖቻችን ገድል ሲወሳ፣ የጀግናው የራስ አሉላ ስም ፣ ባንድ ሁለት ቃልም እንኳን ቢያንስ አለመነሳቱ ግን: እውነት ለመናገር ሳይገርመኝ እንዳላለፈ ማስታወስ አለብኝ! እንዳው እንደዋዛ ታሪክ ባለማወቅ ተረሳ ብዬ ማመን ያቅተኛል! ለምን ? ምክንያቱም፣ እኛ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያውያን አውቀንም ይሁን ሳናውቀው አስክዛሬም ድረስ የቅኝ ገዥዎች ተንኮል ሰለባ የሆን ስለሆነ ነው እላለሁ! የኢትዮጵያን ሃገራዊ ለዑላዊነትና ኢትዮጵያ እንደ አንድ ሃገር የምታሳየውን መንግሥታዊ እድገት ለመግታት ከዘመናት በፊት የነደፉት፣ ይህ ስር የሰደደ የባዕድ ሃይሎች ተንኮል፣ በዚህ እድገት ውስጥ ለየት ያለና ዓይነተኛ ሚና የተጫወቱትን ማህበረሰቦች፣ በተለይ የአማራውን፣ የትግራዩንና የኦሮሞውን ማህበረሰቦች ከስረመሰረቱ እንዲናጉ ማድረግ ሰለሆነ፣ ያሁኑ ትውልድ የዚህ ሰለባ እንደሆነ ስለማውቅ ነው! ስለሆነም ከሚኒሊክ ያላነሰ፣ ራሳቸው ባዕድ ሃይሎች ሳይቀሩ የሚያደንቋቸውን ጀግናው ራስ ዓሉላ አባነጋን የዓድዋ ድል ገድል ሲወሳ "መርሳት" ከባድ ስህተት ነው! ይህም የታላቁ ሚኒሊክ ያንድነትና የ"አንድ-አርጋቸው" መንፈስንና የፖለቲካ ብልህነትንም ፍጹም የሚጻረርና የ መ-ከ-ፋ-ፈ-ል ሰለባ መሆን ስለሆነ ሃገርወዳድ የሆን ሁሉ መጠንቀቅና ማሰብ አለበን ብየ አምናለሁ!!!
አንድ ሁለት ሃሳቦች ለመመልከት:- http://www.goolgule.com/human-ethiopia-life/
ስለ ራስ አሉላ አባነጋ:- http://nazret.com/blog/index.php/2009/03/01/ethiopia_ras_alula_dead_an_abyssinian_ge
http://en.wikipedia.org/wiki/Ras_Alula
http://en.wikipedia.org/wiki/Battle_of_Adwa
No comments:
Post a Comment