ጉ ዞ አ ች ን
ትልቁ የዘመናችን ተመራማሪ፣ ኣይንስታይን የሚባሉት፣
"ነገሩን ቀላል አድርግ፣ ከዚህ በታች ብቻ ግን አታቅለው" አሉ ይባላል።
"Make it simple but not less simpler" /Einstein
የኛንም ጉዳይ እስቲ ቀላል አርገን እንየው፥
*
(ዘና ብለን እዚህ ያለውን ውቡ የምንጭ ስዕላዊ ድምፅ እያደመጥን፤ ለባለቤቱ ከምስጋና ጋር!)
ሥራችን
ሕብራዊነት፣
መጠሪያችን
ሕብራውያን፣
ከሕብረት ሌላ የምንሻው ነገር የለምና።
*
ዓላማችን
ሰብዓዊነትና ኢትዮጵያዊነት።
*
መመሪያችን
ወዳጅ ብቻ ማፍራት፣ እንደፈጣሪያችን ጠላት የለንምና!
እና ም፣
ወዳጃችን
ወዳጃችን ነው፤ የትም አይሄድብንም፤
ጠላታችን
ግን ወዳጃችን ይሆናል።
*
ጉዞአችን
ጠላታችንን ወዳጅ ለማድረግ፣
ሰው
ለማድረግ ነውና።
መጽሀፉም፣ ታላቁ መምህራችንም፣ ጠላትህን ውደድ ሲል፣ነው፣የምናውቀው።
ስለሆነም
ጠላት፣
የለንም።
ታሞም ይሁን ተሳስቶ ጠላት ልሁንላችሁ፣ ሲል የሚቀባጥረውን
ሃሳቡን
ግን
አንወድለትም፤
ሰው እስኪሆን ድረስ፣
በትዕግስትም፣በምሬትም፣ በርጋታም፣ በማስተማርም፣ በትጋት እንነግረዋለን።
ጠላት ስለሌለን፣
ፍርሃትንም
አናውቅም!
*
ወገናዊነታችን
ለምንጩ፣
ለቃል፣ ለሃሳቡ፣
ሕብረ፥ቅላጼ
ለሆነው!
*
መሳሪያችን
ድምጻችን፣
ለዕውነት፣ ለቁም፥ነገር የቆመው ሃሳባችን።
*
ዘዴያችን ግልጽ ነው!
ሰብዓዊነት ና ኢትዮጵያዊነት
ሲነካብን፣
ድምጻችንን
ሳይሸሽጉ ከፍ አርጎ ማሰማት።
*
አጋራችን
እራሳችን ፣ በራሳችን መተማመናችን፣ ሸኝ ቤት አያስገባ ነውና።
*
ቤታችን፣
ኢትዮጵያ
መርኅችን፣
ሕብረ፥ቅላጼ
*
ያም ሲቀልስ፣ ይህም ሲቅልስ፤ ያም ይህም ሲቀላልስ ሕብራዊነትን ተክነን፣
ክብራችንን
ዛሬ ካላስመለስን ነገ የሚጠብቅን አዲሱ ባርነት ብቻ ነውና!
እስካሁን፣
ቄሱም ዝም፣ ሼኩም ዝም፣ ሊቁም ዝም፣ ቄሳሩም ዝም ዝም ሆነና የሁሉንም መለዮ ጠቅልለን እንነሳለን።
ሃገርም ህዝብም
መዘረፍ ከጀመረ እነሆ ሰንብቶ አድሯል። ማደሪያ ጠፍቷል፣ የሚላስ የሚቀመስ አሯል።
*
ለእህል ሳይሆን፣ ለትእግስት፤ ሆደ፥ሰፊው፤ ዝምተኛው ሰፊው አብዛኛው ሰው የምንባለው።
አውሎ ንፋስ ሲመጣ እንደሰንበሌጥ ትኝት የምንለው፣ ቀባጣሪም ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል፣ እስቲ ይሁና ብለን በትእግስት የምናልፈው፣ ጊዜያችን የመጣ ዕለት ግን፣ እንደ አንድ ሰው ሆነን፣
መሬት የምናንቀጠቅጠው፣ሃገር፥ምድር የምንደባልቀው፣ ሕዝበ፥መሬት የምንባለው፣ነን።
አባሪያችን፣ ወገናችን፣ አባላችን፣ ሁሉም ነው።
ዘር አይመርጥ፣ ሃይማኖት አይለይ፣ ሥልጣን አይል፣ ታዛዥ አይል፣ ወጣት አይል አዛውንት አይል።
! ሕብረ፥ቅላጼዋ ሙ ልት የምትልበት ዕለት !
*
ወገናዊነቱ ለምንጩ፣
ማንነቱ፣ ኢትዮጵያዊነቱ ና ሰብዓዊነቱ
ብቻ!!!
***
*
*
ልቦና ያለው ይዘን ፣ሕሊና ያለው ያስብ ፣ የቸገረው ይመከር!
ሁሉም የተሳነው፣ የሰው ያለህ ይበልና ሕብረ፥ቅላጼን ይረዳ!
!
ይህም ላልሆነለት፣
ይለገሰው ተረት፤
ኧረ እስክመቼ ! እያለ ይሰንብት
ጨውም ጨው ካልሆነ፣ ከድንጋይ አይለዩት!
አልማዝ እንኳን አሉ ፣ ቢወረወር በረት፣
ማን አይቶት ፣ማን አውቆት
ማንስ ሊጓጓለት!
*
ከልብ ካዘኑማ መች ይገዳል እምባው፣
ማሰብ ለጀመረ ህይወትም ቀላል ነው፤
በጣት ይቆጠራል ሃይለኛ ሚያደርገው፣
***
[[posterous-content:wAArujBqqdhzperofaCp]]
No comments:
Post a Comment