...
Be Authentic; Go Ahead and Remain Genuine!
May the wind always be at your back.
May the sun shine warm upon your face,
and rains fall soft upon your fields.
And until we meet again,
May God hold you in the palm of His hand.
እያሳሰበንና እያሰጋን ያለው፣ እንደ ልማቱ ሁሉ የሕዳሴው መፈክርና በዋነኝነትም የሕዳሴው ዕቅድ በዴሞክራሲና በሰብዓዊ መብት፣በፍትሕ ማጠናከርና ማስከበር ዙርያ እየተደመጠ አለመሆኑን ነው፡፡ለምን የሚል የመገረም ጥያቄም እንድናነሣ እያደረገን ነው፡፡
......
ኢሕአዴግ ራሱን ብቻ እያዳመጠ ራሱን ማታለል የለበትም፡፡ የፕሬስ ነፃነት በኢትዮጵያ ተረጋገጠ፤ ተከበረ፤ ሲሉት፣አታጭበርብሩኝ! አልቀበልም! ማለት አለበት፡፡ ያለው እኮ፣በመንግሥት ሞኖፖል የተያዘ ፕሬስ ነው፡፡ ያለው እኮ፣ ሕዝብን ነፃ ሆኖ ማገልገል ያልቻለ የመንግሥት ሚዲያ ነው፡፡ .... ....
. .. . ገንዘብ ሲናገር ፍትሕ ዝም የሚልበት፣ ተጠያቂነት የሌለበት ሁኔታ ነው፡፡
ሙስና ከአሰቃቂ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ ... ...
.. .. ... ፓርቲውም ሆነመንግሥት ሊቆጣጠራቸው አለመቻሉና መደናበሩም ስላለ ነው፡፡
ሐቀኞች ሲደናበሩና ሲጃጃሉ ምላጮቹ ተጠናከሩና ተረባረቡ፡፡
ይህን ለማስተካከል ኢሕአዴግ ቆም ብሎ ማሰብና ለማስተካከልም መወሰንና መቁረጥ አለበት፡፡ አማራጩ መንገድ ወይ ተስተካክሎ ተጠናክሮ መቀጠል፣ አልያም ተልፈስፍሶና ተሽመድምዶ መውደቅ እንደሆነ ኢሕአዴግ ሊገነዘበው ይገባል፡፡ ወይ ታሪክ ሠርቶ ማለፍ፣አልያም የራሱን ቃልና መሐላ ረግጦና ደምስሶ ማለፍ እንደሆነ ሊታሰብበት ይገባል፡፡
ማስተካከል ከተቻለ ጊዜው ይፈቅዳል፡፡ ይቻላል፡፡ ግን ቆራጥ አመራርያስፈልጋል፡፡ በቁርጠኝነት ከተወሰነ ደግሞ አቅጣጫው ቀላል ነው፡፡የልማት ሕዳሴ እንደታወጀ ሁሉ፣ የዴሞክራሲና የፍትሕ ሕዳሴምእውን ማድረግ ነው፡፡ ለልማት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ ጅምሩ ሲተገበር፣ ለዴሞክራሲና ለፍትሕም በሕገ መንግሥቱ ላይ መሠረቱ ተቀምጧል፤ ተግባሩን ዛሬውኑ፤ አሁኑኑ ቀጥሉ ማለት ነው፡፡
ከልማትነት መፈክርና ዕቅድ ጋር የዴሞክራሲነትና የፍትሐዊነት መፈክርና ዕቅድም አሁኑኑ! ተግባሩም ዛሬውኑ!!
No comments:
Post a Comment