- -

ከሃይል ንቀት ወደ ዕውቀትና ንቃት ለህዝባዊ ዕድገት

ዕው

ስማ ስሚ ስሙ በስመ አብ ቢስሚላሂ በሉ፤

በቅላጼ መልክት፤ ይታደስ-ይቀደስ ትውልደ-ብርሃኑ፤

በተቻለው መጠን፤ በተፈለገ ለት፤ ቀን ይወጣል አሉ።

እንደ መሃል ምሥራቅ፤ አፍሪቃ ሰሜኑ፤

ኢትዮጵያም ይደርሳል ፅዋው መኅበሩ፤

Beautiful Minds of Addis Tiwlid 2012 1*)

Search

Thursday, May 12, 2011

‹‹ምነው እንደ ጋዳፊ አልወርድም አልክ›› | Reporter Amharic

Interesting stories from "Reporter Amharic"; "Kibur Mnister"/ "Y.E. Minister"- ክቡር ሚኒስትር  columnist:

ክቡር ሚኒስትር  

[ክቡር ሚኒስትሩ በቤተ መንግሥት ለግብፅ ልዑካን በተዘጋጀ ግብዣ ላይ ተገኝተዋል፡፡ ከእንግዶቹ ጋርም ያወራሉ፡፡]

-    ታህሪር አደባባይ ላይ ከአብዮተኞቹ ጋር ሆነሽ ስትጮሂ መልክሽን ያየሁት መሰለኝ፡፡
-    አዎን ክቡር ሚኒስትር ከዚያው ነበርኩ፡፡ ነበርኩ ነው፣ ከረምኩ የሚባለው? ዋና ተሳታፊም ነበርኩ፡፡
-    መልካም ነው. .  ትግላችሁም ውጤት አስገኝቷል፡፡
-    አዎን ሙባረክን አባረርን፡፡ ለእስርም አበቃን፡፡
 

Read More:

ይቀጥል ይቀጣጥልና አሰማምሮ ይደመድማል

[የስብሰባው ቀን ደረሰ፡፡ ግርግር ተፈጠረ፡፡ ቀደም ብሎ የተበተነው የቀኑ ፕሮግራም ሌላ፤ አሁን የተበተነው ሌላ ሆነ፡፡ ሰብሳቢው ሌላ ተናጋሪዎችም ሌላ ሆኑ፡፡ ክቡር ሚኒስትር ስብሰባውን ይከታተሉት ነበር፡፡ በቴክስት መሴጅ]
-    እሺ እንዴት እየሔደ ነው?
-    ችግር የለም በቁጥጥር ሥር ነው፡፡ ሰብሳቢው የእኛ ሆኗል፡፡
-    በጣም ጥሩ . .  .ተቃውሞ አለ?
-    አለ፤ ግን የትም አይደርስም?
-    ሰብሳቢው አጀንዳው ቢቀያየርም እኔ እቀጥላለሁ ብሎ ማይክራፎኑን አልለቅም ብሏል፡፡
-    ቤቱ ምን አለ?
-    እየተቃወመ ነው፡፡
-    ምን ብሎ?
-    ‹‹ምነው እንደ ጋዳፊ አልወርድም አልክ›› እያለ ይስቃል፡፡
-    መሳቁን እንደፈለጉት ይሳቁ፡፡ እንትና ጣልቃ እንዳይገባ ግን ተጠንቀቁ፡፡
-    ማን?
-    !  N A T O!

 **************

More from " ክቡር ሚኒስትር":

[የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርብ ለማየትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመወያየት የአውሮፓ ልዑካን አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋርም እየተነጋገሩ ይገኛሉ]     እንግዶቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡
....

[ምሳ ሰዓት ደርሶ ክቡር ሚኒስትሩና እንግዶቹ በቦታው ተገናኝተዋል፡፡ አጀንዳው ግን የተላለፈው ዜና ነበር፡፡]
-    እንዴት ነው ነገሩ ክቡር ሚኒስትር - እኛ ጫማ ሥር ወድቀን ይቅርታ ጠይቀናል እንዴ?
-    አልጠየቃችሁም የተላለፈው ዜናም ስህተት ነው፡፡ በአስቸኳይ እንዲታረምና ይቅርታ እንዲጠየቅም ታዟል፡፡
-    መታረሙና ይቅርታ መጠየቁ ጥሩ፤ ነገር ግን ምን ዓይነት ሙያና ሥነምግባር ያላቸው ሰዎች ናቸው እንዲህ ብለው የሚሠሩት፡፡
-    አሁን ወደመጣንበት አጀንዳ እንግባና እንቀጥል፤ ያኛው እንኳን ለእናንተ ለእኛም አስደንግጦናል፡፡ ሙሉ መልስ ይዤ እነግራችኋለሁ፡፡
-    እሺ እንቀጥል፡፡
-    የተከበራችሁ የአውሮፓ እንግዶቻችን ኢትዮጵያና አውሮፓ የረዥም ጊዜ ግንኙነት አላቸው፡፡ በችግርም ሆነ በደስታም አብረን ተሰልፈናል፡፡ አሁንም በሽብርተኝነት ዘመቻው ላይ አብረን ነን፡፡ እናንተ ግን ይህን ሐቅ ችላ እያላችሁ ከተቃዋሚዎች ጋር ተሰልፋችኋል፡፡ እነሱ የሚሉትን ታዳምጣላችሁ፡፡ እኛ የምንላችሁን አታዳምጡም፡፡
-    ክቡር ሚኒስትር እነሱ ያሉትን አናዳምጥም፡፡ እንዲያውም አሁን አሁን ለመሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲ በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ወይ? ብለን እስከመጠየቅ ደርሰናል፡፡ ነገር ግን የሰብዓዊ መብት፣ የፕሬስ ነፃነት፣ በአጠቃላይ የዴሞክራሲና የፍትሕ ጉዳይ በእጅጉ እያሳሰበን መጥቷል፡፡
[ውይይቱ በጥሩ መንፈስ ቀጥሎ የማጠቃለያው ስብሰባ በነጋታው እንዲካሔድ ተወስኖ ስብሰባው ተበተነ፡፡ ክቡር ሚኒስትርም ማታ ቤታቸው ገብተው እንደገና ዜና ለመከታተል ተመቻችተው ተቀመጡ፡፡ ዜናውም መጣ፡፡ እንደገና አበዱ]

Read More:


...
-    እኔ?
-    አዎን እርስዎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
-    አሁን በዚህ ሁለት ቀን ያየሁትኮ አገርንና ሕዝብን የሚጎዳ አደገኛ አካሔድ ነው፡፡
-    የቆየ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
-    እና አንተ የኢሕአዴግ አባል እያለህ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ኢሕአዴግ ናቸው ትላለህ?
-    ናቸው አላልኩም . . . ብዬም አላውቅም፡፡
-    አልገባኝም፡፡
-    ክቡር ሚኒስትር በእኔ አመለካከት ኢሕአዴግ ውስጥ ሁለት ዓይነት ፓርቲ አለ፡፡
-    ኢሕአዴግ ውስጥ ሁለት ዓይነት ፓርቲ አለ ነው ያልከው?
-    አዎን ሁለት ዓይነት ፓርቲ አለ፡፡
-    ገዢ ፓርቲ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ሌላ በውስጡ ምን ዓይነት ፓርቲ አለ ልትለኝ ነው?
-    ከገዢው ፓርቲ ጎን ለጎን ተቃዋሚ ፓርቲ በውስጡ አለ፡፡
-    ተቃዋሚ ፓርቲም፣ ገዢ ፓርቲም በኢሕአዴግ ውስጥ አለ ነው የምትለኝ?
-    አዎን! ሁሉንም በውስጡ ያቀፈ ፓርቲ ሆኗል፡፡
-    እንደዚህ ዓይነት ፓርቲ ምን የሚሉት ፓርቲ ነው?
-    ‹‹ዋን ስቶፕ ሾፕ ፓርቲ››

No comments:

Post a Comment

1*)


"When the idea formed of Divinity is the fruit of true spiritual culture, its intimate re-action on the inner perfection is at once beneficial and beautiful. All things assume a new form and meaning in our eyes when regarded as the creatures of forecasting design, and not the capricious handiwork of unreasoning chance. The ideas of wisdom order, and adaptative forethought,—ideas so necessary to the conduct of our own actions, and even to the culture of the intellect,—strike deeper root into our susceptible nature, when we discover them everywhere around us. The finite becomes, as it were, infinite; the perishable, enduring; the fleeting, stable; the complex, simple,—when we contemplate one great regulating Cause on the summit of things, and regard what is spiritual as endlessly enduring. Our search after truth, our striving after perfection, gain greater certainty and consistency when we can believe in the existence of a Being who is at once the source of all truth, and the sum of all perfection. The soul becomes less painfully sensible of the chances and changes of fortune, when it learns how to connect hope and confidence with such calamities. The feeling of receiving everything we possess from the hand of love, tends no less to exalt our moral excellence and enhance our happiness. Through a constant sense of gratitude for enjoyment—through clinging with fond trustfulness to the object towards which it yearns, the soul is drawn out of itself, nor always broods in jealous isolation over its own sensations, its own plans, hopes, and fears. Should it lose the exalting feeling of owing everything to itself, it still enjoys the rapture of living in the love of another,—a feeling in which its own perfection is united with the perfection of that other being. It becomes disposed to be to others what others are to it; it would not that they too should receive nothing but from themselves, in the same way that it receives nothing from others."

Wilhelm von Humboldt, The Limits of State action; 1792(CHAPTER VII.
Religion)

The Synthesis